Irrigation and Drainage Research and Design

 

የመስኖና ድሬኔጅ ጥናትና ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

  • የክልሉን የውኃ ሀብት ለመስኖ አገልግሎት ለማዋል የጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን ያከናውናል ወይም በሌሎች ያሠራል፣ቁጥጥር ያደርጋል፤
  • አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመመካከር በክልሉ ውስጥ በተለይም ቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የመስኖ ልማት አቅም ለመለየት ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣ የውሀ እቀባና የአነስተኛ፣ የመካከለኛ እና ከፍተኛ መስኖ ፕሮጀክቶችን የጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን ያከናውናል፣ እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ የአካባቢውን የግብርና መሬት ለማልማት የሚያስችል የመስኖ ልማት ፕሮግራሞችን ይቀርፃል፣ ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፤
  • በፌደራሉ መንግሥት ባለቤትነት በክልሉ ውስጥ ለሚካሄዱ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ክንውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፣ ውክልና ሲሰጠው የግንባታ ክትትል ሥራ ይሠራል፣ ያሠራል፤
  • በመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ጥናት የመስኖ ውኃ ተጠቃሚው ተሳታፊና  እንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • በክልሉ ውስጥ በጎርፍ አደጋ የሚጠቁ አካባቢዎች ቅድመ-ጥናት ያካሂዳል፣ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን ይሠራል፡፡
  • በክልሉ ውስጥ በግብረ ሠናይ ድርጅቶ የሚካሄዱ የመስኖና ድሬኔጅ ጥናትና ዲዛይን ስራዎች በመፈተሽ ወደ ስራ እንዲገቡ ፈቃድ ይሰጣል፣
  • ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  • ከመስኖና ድሬኔጅ ጥናትና ዲዛይን ሥራዎች ጋር የተያያዙ ቴክኖሎጅዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል፣ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በመፈተሽ ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል፣ ስልጠና ይሠጣል፤
  • በዞኖችና በወረዳዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ይቆጣጠራል፤ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት አሠራሮችን ይዘረጋል፡፡
Scroll to Top