የመስኖ ተቋማት አጠቃቀም፣ አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት
- ማህበራት ስለሚደራጁበት፣ አቅማቸው ስለሚገነባበትና ስለሚጠናከሩበት ሁኔታ በጥናት ላይ ተመሥርቶ ስልቶችን ያመነጫል፣ ልዩ ልዩ ስትራቴጅዎችን፣ መመሪያዎችን እንዲሁም የመገልገያ ሰነዶችን ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤
- በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን የመስኖ ተጠቃሚዎች ማኅበራትን ወይም ፌዴሬሽን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎችንና የማህበራት መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ-ደንቦችን መሠረት በማድረግ ያደራጃል፣ ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- ከማኅበራት መቋቋምና ተግባራቸውን ከማከናወን ጋር በተያያዘ ለዞንና ወረዳ አስፈጻሚ አካላትና ማህበራት የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ይሠራል፤ የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፤
- በክልሉ መንግሥት አማካኝነት የተገነቡ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የመስኖ ግድቦችን፣ ቦዮችንና ሌሎች የመስኖ አውታሮችን ተረክቦ ያስተዳድራል፣ ይንከባከባል፣
- በክልሉ ውስጥ የተገነቡ የመስኖ ተቋማት ዘላቂና ተፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የመለስተኛና ከፍተኛ ጥገና ሥራዎችን ያከናውናል ወይም በሌሎች ያሠራል፣ የጥገና ስራው ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል፣ሲጠናቀቅ ከገንቢው አካል ተረክቦ ለመስኖ ውኃ ተጠቃሚዎች ማህበራት ያስረክባል፤
- የግንባታቸው የአገልግሎት ዘመናቸው አልቆ አገልግሎት የማይሠጡ የመስኖ ቋማትን የመልሶ ጥናትና ግንባታ ስራዎችን ይሠራል፤
- በፌደራሉ መንግሥት ባለቤትነት በክልሉ ውስጥ ለሚካሄዱ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ክንውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፣ ተቋማትን ተረክቦ ያስተዳድራል፣
- አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመመካከር በክልሉ ውስጥ በተለይም ቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የተገነቡ የውሀ እቀባ፣ የአነስተኛ፣ የመካከለኛ እና ከፍተኛ የመስኖ የመስኖ አውታሮች የጥገና ሥራዎችን ያካሂዳል፣
- የመስኖ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከአስገንቢው አካል ጋር ርክክብ ይፈጽማል፤ የመጠቀም ጥያቄ ላቀረቡ ማህበራት ያስተላልፋል፡፡ ደህንነታቸውን ይቆጣጠራል ተገቢውን ጥገና በወቅቱ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- በከፍተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ለአጠቃቀም እና አስተዳደር በሚያመች ሁኔታ እንዳስፈላጊነቱ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ይከፍታል፣ የተቀናጀ የልማት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሠራል፤
- ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- ከመስኖና ድሬኔጅ ተቋማት አስተዳደር ሥራዎች ጋር የተያያዙ ቴክኖሎጅዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል፣ አዳዲስ አሠራሮችን ይዘረጋል፣ ቴክኖሎጅዎችን በመፈተሽ ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል፣ ስልጠና ይሠጣል፤
- ሁለትና ከዚያ በላይ ዞኖችን በሚያገለግል የመስኖና ድሬኔጅ አውታር ላይ ማህበራት እንዲመሠረቱ፣ እንዲደራጁና ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ተከታታይ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የምዝገባ ጥያቄ ለሚያቀርብ ማህበር ለምዝገባ የሚያበቃዉን መስፈርት ያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ በመስኖ ዉሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት መዝገብ ዉስጥ በመመዝገብ ለማህበሩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይሠጣል፤
- የተቋቋሙ የመስኖ ውኃ ተጠቃሚዎች ማህበራትን የሕግና የፋይናንስ ቁጥጥርና ምርመራ ያደርጋል፤
- ማህበራት በተቀመጠላቸው አሠራር መሠረት በአግባቡ መንቀሳቀሳቸውን እና ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣታቸውን ለማረጋገጥ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ምርመራ ያደርጋል፤ በውጤቱም መሠረት ለጠቅላላ ጉባኤ እያቀረበ ተገቢው እርምጃ መወሠዱን ያረጋግጣል፤
- በዞኖችና በወረዳዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ይቆጣጠራል፤ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት አሠራሮችን ይዘረጋል፡፡
- አንስተኛ_መስኖ_ፓምፕ_ማስተላለፊያና_ብድር_አመላላስ_መመሪያ_53_2015.pdf
- ከጸደይ_ባንክ_ጋር_የፓምፕ_ስርጭት_ስምምነት.pdf
- የመስኖ_መሳቢያ_ፓምፕ_ስርጭትና_አጠቃቀም_ረቂቅ_መመሪያ.pdf
- የመስኖ_ማህበራት_ሂሳብ_አያያዝ_መመሪያ_239_2008.pdf
- የማህበራት_ኦዲት_ቁጥጥር_መመሪያ_239_2008.pdf