የዕቅድ፣ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት
- የተቋሙን የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ከሚመለከተው ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ያስገመግማል፤
- የተቋሙን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ያስገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤
- የበጀት ምደባ፣ ግምገማና አፈጻጸም ይከታተላል፤
- የበጀት ዝውውርን መመሪያን መሠረት አድርጎ ያዘጋጃል፣ እንዲጸድቅም ክትትል ያደርጋል፤
- አጠቃላይ የፊዚካልና የፋይናንሻል አፈጻጸምን ከቢሮው ዕቅድ ጋር አያይዞ ክትትል ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት በመዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
- የመስኖ ልማት መረጃና ኢንፎርሜሽን ሥርዓትን ይዘረጋል፣ ያደራጃል፣ መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል በየወቅቱ ያስተላልፋል፤
- የቢሮውን የኤሌክተሮኒክስና መገናኛ መሳሪያዎችን ደረጃ ያወጣል፣ ግዥ ሲፈጸም በደረጃጀቸው መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የቢሮው የኤሌክትሮኒክስና መገናኛ መሳሪያዎች ደህንነት እንዲጠበቁ የጥገናና የስርዓት ማሻሻል ስራዎችን ይሠራል፤
- ከህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጋር በመሆን ለማህበረሠቡ የሚቀርቡ መረጃዎችን ያሳልጣል፤
- ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤