በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለዉ የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ
በሀገሪቱ የተነደፈዉን የአስር ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ በብሔራዊ ክልሉ ልማት ዉስጥ ሊኖረዉ የሚገባዉን ድርሻ በዓይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ለማድረግና የህዝቡን የላቀ ተሳትፎ ይበልጥ በማሳደግ ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚነቱን በተጨባጭ ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ በክልሉ ዉስጥ የተቋቋሙት የተዋረድ አስተዳደር እርከኖች እርስ በርስ ተቀናጅተዉ የሚመሩበትን ስርአት ከማዘመን ጎን ለጎን የክልሉ ኢኮኖሚ ስፋት፣ ዉስብስብነትና ፍጥነት በሚጠይቀዉ መጠን መንግስታዊ ተቋማትን ፈትሾ እንደገና ለማደራጀት፣ በብቃት ለመምራትና ለመደገፍ የሚያስችል ቁመና ያለዉ ተቋም እዉን በማድረግ በማስፈለጉ፤
⇒ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለዉ የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም