የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት
በየበጀት ዓመቱ፡-
- የፋይናንስ ኦዲት ያደርጋል፣
- የንብረት አስተዳደርና አያያዝ ኦዲት ያደርጋል፤
- የኦዲት ግኝትን መሠረት በማድረግ አዳዲስ አሠራሮችን ዘርግቶ ምርመራ ያደርጋል፣ በአሠራር እንዲመለሱ ያደርጋል፤
- የኦዲት ግኝቶችን መሠረት በማድረግ ከጠቅላይ ኦዲት ጋር በመሆን አጠቃላይ የተጠያቂነት አሠራር እንዲሠፍን ያደርጋል፤
- ቢሮው ውስጥ ከፍተኛ ሀብት በሚጠይቁ ተግባራትና ችግር ለፈጠሩ በሚችሉባቸው ክንዋኔ ላይ የተለየ የኦዲት ስርዓት በመስራት ሀብት እንዳይባክን ያደርጋል፣ ተጠያቂነትም እንዲሰፍን ይሠራል፤
- አጠቃላይ የውስጥ ኦዲት አሠራር የክልሉን የኦዲት አሰራር፣ የፕሮጀክቶችንና የፕሮግራሞችን የሀብት አስተዳደር መመሪያ መሠረት አድርጎ ይፈጽማል፤
- ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤