የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

  • ስለክፍያ  በክልልም ሆነ በዞን የመስኖና ድሬኔጅ ጥናትና ዲዛይን ወይም ግንባታ ስራ እንዲያከናውን ኃላፊነት ተሠጥቶች ውል የያዘው አካል በውሉ መሠረት ክፍያዎችን ይፈጽማል፤ በውል አስተዳደሩ ሂደቱ የሚፈተሩ ችግሮችንም በኃላፊነት ይዞ መፍትሄ ይሠጣል፤
  • በቢሮው የሚታዘዙ የመስኖና ድሬኔጅ የግንባታና የአማካሪ ክፍያ ሠነዳቸው መሟላቱን እያረጋገጠ በጊዜው ክፍያ ይፈጽማል፤
  • በቢሮው የሚታዘዙ  ሌሎች ክፍያዎችን መመሪያን መሠረት በማድረግ በጊዜው ክፍያ ይፈጽማል፤
  • የሂሳብ የወጭና ገቢ የሂሳብ ሰነዶችን ከውስጥ ኦዲት፣ ከዕቅድ ዝግጅት እና ከባንክ ጋር ይናበባል፣ ሪፖርት አዘጋጅቶ በየ15 ቀኑ ለቢሮ ኃላፊው ያቀርባል፤
  • የቢሮውን ንብረትና ተሸከርካሪ በተቀመጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት መዝግቦ ይይዛል፣ በየ3 ወሩ ያለውን ንብረት ለቢሮ ኃላፊው በሪፖርት ያሳውቃል፤
  • ማንኛውንም ከንብረትና ፋይናስ የተገናኘ ሰነድ በአግባቡ ይሠንዳል፣ ሲጠየቅም ያቀርባል፤
  • አጠቃላይ የፋይናንስና ግዥ አሠራር የክልሉን የገንዘብ ቢሮ የአሠራ መመሪያ፣ የፕሮጀክቶችንና የፕሮግራሞችን የሀብት አስተዳደር መመሪያ መሠረት አድርጎ ይፈጽማል፤
  • ለቢሮው የሚያስፈልጉ የቁስ እና የአገልግሎት ግዥዎችን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያፀድቃል፣ መመሪያን መሠረት አድርጎ ግዥ ይፈጽማል፤
  • በተቋሙ ውስጥ አገልግሎት የማይሠጡ ቁሶችን ያስጠናል፣ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የሚወገዱበትን አግባብ ያመቻቻል፤
  • ከፋይናስና ንብረት አስተዳደር ጋር በተገናኝ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን ይነድፋል፣ እንዲተገበሩም ለቢሮ ያቀርባል፤
  • ቢሮው የተቋቋመበትን ዓላማ ያሳካ ዘንድ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት የተሽከርካሪ ስምሪት ይሠጣል፤
  • የተሸከርካሪ ስምሪት አሠራር እያዘጋጀ በቢሮው ያፀድቃል፤
  • የነዳጅ አጠቃቀም ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲፈጸም አሠራር ይዘረጋል፤
  • ተሸከርካሪዎች ወቅታዊ ጥገናና ፍተሻ እንዲያገኙ ያደርጋ፣ የክልሉን የመንገድ ትራንስፖርት መመሪያ በሚያዘው መሠረት ሌሎች ተግባሮችን እንዲፈጸሙ ያደርጋል፤
  • ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  1. Proclamation_No_179_2011_The_Amhara_National_Regional_State_Procurement.pdf
  2. Proclamation_no_178_2011_revised_finance_administration_proclamation.pdf
  3. ANRS BoFED Budget Admin Guidelines 8 2004.pdf
  4. ANRS BoFED Disbursement Guidelines 5 2004.pdf
  5. ANRS BoFED Cash mgt 4 2004.pdf
Scroll to Top