የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

  • አጠቃላይ የተቋም ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም አሰራርና አፈጻጸሞችን ለማህበረሰቡ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መረጃ ይሰጣል፤
  • የትኛውም በመንግስት በጀት የሚመሩ የቢሮው መድረኮችና ስልጠናዎች ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጀምሮ ለመድረኩ ስኬታማነት ሃላፊነት ወስዶ ያስተባብራል፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአጋር አካላት መድረኮችን ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የተጠናቀቁ  የመስኖ ግንባታ ርክክቦች እና የምርቃ ስነስርዓቶችን ያስተባብራል፤
  • በመረጃ ነጻነት አዋጅ መሰረት ማንኛውም የተቋሙን አሰራር አስምልክቶ ለሚዲያ አካላት እና ለማህበረሰቡ ግልጽ መረጃ የሚያገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • በየደረጃው መፈታት ያልቻሉ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ የሚነሱ የማህበረሰብ ቅሬታዎችን እና አቤቱታዎች የሚፈቱበትን መንገድ ያመቻቻል፤
  • ቢሮው በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ የተሻለ ተሞክሮዎችን በመቀመር እንዲሰፉ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይሠራል፤
  • በመስኖና ድሬኔጅ ዙሪያ በማህበረሰቡና በተቋሙ ውስጥ ያሉ ዕውቀቶችንና ልምዶችን በማሰባሰብ ከአዳዲስ አሰራሮችና እውቀቶች ጋር የሚጣመሩበትንና የሚሸጋገሩበትን አግባብ ያስተባብራል፤
  • ሌሎች ከመስኖና ድሬኔጅ ጋር የተገናኙ የህትመት ውጤቶችን ለማህበረሠቡ ያደርሳል፤
  • ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  1. አጠቃይ ተቋማዊ የአሰራር መመሪያ.pdf
  2. ከክፍያ_በፊት_የሚረጋገጡ_ሰነዶች_መመሪያ.pdf
Scroll to Top