Irrigation Drainage Construction Supervision

 

የመስኖና ድሬኔጅ ግምባታና ክትትል ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

  • የክልሉን የውኃ ሀብት ለመስኖ አገልግሎት ለማዋል የግንባታ ሥራዎችን ያከናውናል ወይም በሌሎች ያሠራል፣ ግንባታቸው ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከገንቢው አካል ተረክቦ ለመስኖ ተቋማት አስተዳደር ያስረክባል፤
  • በፌደራሉ መንግሥት ባለቤትነት በክልሉ ውስጥ ለሚካሄዱ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ክንውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፣ ውክልና የግንባታ ሥራዎችን ይሠራል፣ ያሠራል፤
  • በመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢው ኅብረተ-ሰብ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • የመስኖ ልማት ሽፋን እንዲያድግ የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
  • በመስኖ ልማት ሥራዎች ለሚሳተፉ አጋር አካላት ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣ የሚገነቡ የመስኖ አውታሮች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
  • አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመመካከር በክልሉ ውስጥ በተለይም ቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የውሀ እቀባና የአነስተኛ፣ የመካከለኛ እና ከፍተኛ መስኖ ግንባታዎችን ያከናውናል፣ እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ የባህላዊ ወንዝ ጠለፋ ሥራዎች እንዲስፋፉ ያበረታታል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
  • በክልሉ ውስጥ በጎርፍ አደጋ የሚጠቁ አካባቢዎች የመከላከያ ግንባታዎችን ይሠራል፣ ያስገነባል፤
  • በክልሉ ውስጥ በግብረ ሠናይ ድርጅቶ የሚካሄዱ የመስኖና ድሬኔጅ የግንባታ ስራዎችን በመፈተሽ ወደ ስራ እንዲገቡ ፈቃድ ይሰጣል፣
  • ለቢሮው ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  • ከመስኖና ድሬኔጅ ግንባታ ሥራዎች ጋር የተያያዙ ቴክኖሎጅዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል፣ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በመፈተሽ ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል፣ ስልጠና ይሠጣል፤
  • በዞኖችና በወረዳዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ይቆጣጠራል፡፡ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት አሠራሮችን ይዘረጋል፡፡
  1. የስራ_ተቋራጮች_የስራ_አፈጻጸም_መመሪያ_ቁጥር_2_2008.pdf
  2. የኢንተርፕራይዞች_ም_ቤት_አደረጃጃት_መመሪያ.pdf
  3. ለጥቃቅንና_አንስተኛ_የስራ_ዕድል_ፈጠራ_መመሪያ_52_14.pdf

 

Scroll to Top