የአማራ ከልል የመስኖ ልማት የአየር ንብረት ለዉጥ ተጽኖን የሚቋቋም ግብርና በመፍጠር በ2022 ለምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች ዋነኛ የምግብ አቅራቢ ሆኖ ማየት፡፡
የህብረተሰብ ፍላጎትን እና የተቀናጀ የዉሀ ሀብት አስተዳደርን መርሆ መሰረት በማድረግ መስኖን ማስፋፋት፤ የመስኖ ኦፕሬሽን እና ጥገና ስረአት ዘመናዊ ማድረግ፤የመስኖ ዉሀ አጠቃቀምን በማሻሻል የግብርና ምርት እና ምርታማነትን ከአየር ንብረት ተጽኖ በመቀነስ ምርትን ዘላቂ በሆነ መንገድ በማሳደግ ድህነትን ለመቀነስ ብሎም ዘመናዊ የመስኖ ግብርና ሴክተርን መፍጠር፡፡
- ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት፤
- የክልሉን ህዝብ የመስኖ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን፤
- መስኖ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን እናረጋግጣለን፤
- የእኛ ተጠቃሚነት የሚረጋገጠዉ ህብረተሰቡ ሲጠቀም መሆኑን እናምናለን፤
- ኪራይ ሰብሣቢነትን በቁርጠኝነት መታገል፤
- ህግን ማክበር፤
- ግልጽነት ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት፤
- ህግ፣ ደንብና መመሪያ ለዉጤት፤
- በቡድን ስራን የመስራት ባህል፤
- የመማማርና የመለወጥ ተነሳሽነት፤
የመስኖ ፖሊሲዉ አጠቃላይ አላማ ዘላቂ የመስኖ ዉሀ እንዲኖር ማስቻል እና አጠቃቀሙን ዘመናዊ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በክልሉ በቤተሰብ ደረጃ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም ድህነትን ለመቀነስ የመስኖ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዲኖረዉ ማድረግ ነዉ፡፡
- የክልሉን የውኃ ሀብት ለመስኖ አገልግሎት ለማዋል የጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን ያከናውናል፣ በሌሎች ያሠራል፣ ግንባታቸው ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለተጠቃሚዎች ያስረክባል፤
- በክልሉ መንግሥት አማካኝነት የተገነቡ የመስኖ ግድቦችን፣ ቦዮችንና ሌሎች አውታሮችን ያስተዳድራል፣ ይንከባከባል፣ ይጠግናል፣ ስለ አጠቃቀማቸውም ዝርዝር የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤
- በክልሉ ወስጥ የተገነቡ የመስኖ ተቋማት ዘላቂና ተፈላጊ አግልግሎት አንዲሰጡ የመለስተኛና ከፍተኛ ጥገና ስራዎችን ያካሄዳል አንዲካሄዱ ያደርጋል፡፡
- አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመመካከር በክልሉ ውስጥ፣ በተለይም ቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የውሀ እቀባና መስኖ ልማት ስራዎችን ያከናውናል፣ እንዲከናወኑ ያደርጋል፣
- በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት ያደራጃል፣ ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- በፌደራሉ መንግሥት ባለቤትነት በክልሉ ውስጥ ለሚካሄዱ የመስኖ እና ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክቶች ክንውን ድጋፍ ያደርጋል፤ በተቀመጠ አሰራር ውክልና ሲሰጠው የጥናት ፤ የግንባታ እና የመስኖ ተጠቃሚዎች ማህበር ማደራጀት ስራ ይሰራል፤
- ከመስኖ ስራዎች ጋር የተያያዙ ቴክኖሎጅዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል፤ አዳዲስ ቴክኖልጅዎችን በመፈተሸ ወደ ስርጭት እንዲገቡ ያበረታታል፤
- በክልሉ ውስጥ በጎርፍ አዳጋ የሚጠቁ አካባቢዎች ቅድመ ጥናት ያካሄዳል ፤ የመከላከያ ግንባታዎችን ያስገነባል፡፡ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ይሰራል ፡፡
- የመስኖ ልማት ሽፋን እንዲያድግ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
- በተቀናጀ የየተፋሰስ ልማት በወሃና ኢነርጅ ቢሮ ጥናት የተለዩ የልል የከርሰ ምድር እና የገፀ-ምድር የውሃ ሃብት ለመስኖ ልማት የሚውልበት ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
- በመስኖ ልማት ስራዎች ለሚሳተፉ አጋር አከላት ሙያዊ ድጋፍ ይሠጣል የሚገነቡ የመስኖ አውታሮች እስታዳርዳቸውን የጠበቁ አንዱሆኑ ተገቢውን ክትትልና ቁጥር ደርጋል፡፡
- በከፍተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ለአጠቃቀምና አስተዳደር በሚያመች ሁኔታ እንዳስፈላጊነቱ ፕሮጅክት ፅ/ቤት ይከፍታል የተቀናጀ የልማት እቅድ ያዘጋጃል ተግባራዊ አንዲሆን ከሚመለከታቸው አካት ጋር ብትብብር ይሰራል፡፡
- በመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተሳታፊና ተጠቃሚ አንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻችል፡፡
- በቆላማ አካባቢዎች ያለውን የመስኖ ልማት አቅም ለመመለየት ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣የአካባበዊውን ግበርና መሬት በማልማት የሚስችል የመስኖ ልማት ፕሮግራሞችን ይቀርፃል ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፡፡
- ከግብርናና ውሃና ኢነርጅ ቢሮዎች ጋር በመተባበር የቆላማ አካባቢዎች ውሃን ማዕከል ያደረጉ የተፋሰስ ልማት ሰስራዎችና የመስኖ ልማቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፡፡
- የመስኖ ልማት መረጃና ኢንፎርሜሽን ስርዓትን ይዘረጋል፡፡
- የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ስራዎች
- የመስኖ ግንባታ ስራዎች
- የተገነቡ የመስኖ ተቋማት አስተዳደርና አስፈላጊውን ጥገና ማካሄድ
- በቆላማ አካባቢዎች በልዩ ሁኔታ መስኖ ልማት ማስፋፋት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡