በክልሉ የመስኖ ልማት መጠቀም የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ ቢሆንም በዘመናዊ መንገድ መስኖን በስፋት መጠቀም የጀመርነው ከ1980ቹ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን በክልላችን በደረሰው ተደጋጋሚ ድርቅ የተነሳ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በአማራጭነት የሚሰራ ሳይሆን የህልውና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅና ችግሩን ከመሰረቱ ለመቀልበስ የሚያስችል ሥራ ለመሥራት የክልሉና የፌደራል መንግስት ለመስኖ ተቋማት ግንባታ የሚመድቡት በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በዚህም መሰረት የዘመናዊ መስኖ አውታር ግንባታ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በተመሳሳይ ደረጃ የተፈጸመ ባይሆንም፤ ሥራው በተሠራባቸው አካባቢዎች ሲታይ የኅብረተብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ እና ለብዙ ዓመታት የቆዩ የኅብረተብ ጥያቄዎችን ከመመለስ አኳያ አበረታች ለውጥ ተመዝግቧል፡፡
የመስኖ መሠረተ ልማት የማስፋፋት ሥራን በተሳካ ሁኔታ ጀምረነው እየሰፋ የመጣና የቆዬ የኅብረተብ ጥያቄን የመለሰ ቢሆንም አሁንም በርካታ የሆነ የክልላችን አካባቢዎች የመስኖ አውታር ግንባታ ሥራ አልተሠራባቸውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኅብረተቡ ጥያቄወች ሙሉ በሙሉ አልተመለሱም፡፡ በክልሉ ሠፋፊ የሆኑ መሬቶችን በመስኖ ማልማት ሲቻል በበጀት እጥረትና በተቋማዊ አቅም ውስንነት የተነሳ የታሰበውን ያህል ማከናወን አልተቻለም፡፡ በሌላ በኩል ተገንብተው ያለቁና ለመስኖ ውኃ ተጠቃሚ ማኅበራት የተላለፉ የመስኖ አውታሮችም ቢሆኑ ብዙ አገልግሎት ሳይሰጡ የሚበላሹ ጥቂቶች ስላልሆኑ ውጤታማ የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፤ ተቋማዊ ለውጥና ጥንካሬ በመፍጠር ችግሩን መፍታት አስፈላጊ ነው፡፡
ከ2018—2022 የ5 ዓመት ዕቅድ —>ANRS BoILLAD Strategic Plan 2018—2022.pdf
በሀገራችን ከተፈጥሮ ዝናብ ውጭ የውሀ ሀብትን ለመስኖ በስፋት መጠቀም የጀመረነው ከ1980 ዓ.ም በኋላ ሲሆን በደረሳ ተደጋጋሚ ድርቅ የተነሳ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በአማራጭነት የሚሰራ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅና ችግሩን ከመሰረቱ ለመቀልበስ የሚያስችል ስራ ለመስራት የክልሉና የፌደራል መንግስት በሚመድቡት በጀት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ በተደረገው ርብርብ በሁሉም አካባቢ በተመሳሳይ ደረጃ የተፈጸመ ባይሆንም ስራው በተሰራባቸው አካባቢዎች የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ እና ለብዙ አመታት የቆዩ የህብረተሰብ ጥያቄዎችንየመለሰ አበረታች ለውጥ ተመዝግቧል፡፡
የመስኖ መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራን በተሳካ ሁኔታ ጀምረነው እየሰፋ የመጣና የቆዬ የህብረተሰብ ጥያቄን የመለሰ ቢሆንም አሁንም በርካታ የሆነ የክልላችን አካባቢዎች የመስኖ አውታር ግንባታ ስራ አልተሰራባቸውም የህብረተሰብ ጥያቄወችም አልተመለሱም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም -> ANRS BoILLD 2017 Annual Plan Final.pdf