ክልል አቀፍ ዘመናዊ የመስኖ ተቋማት ቆጠራ እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለመዘርጋት የሁለትዮሽ ሥምምነት ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።

ሚያዚያ22/2016ዓም

ክልል አቀፍ ዘመናዊ የመስኖ ተቋማት ቆጠራ እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለመዘርጋት የሁለትዮሽ ሥምምነት ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።

ሚያዚያ22/2016ዓም
ባህርዳር
የአብክመ መስ/ቆ/አካ/ል/ቢሮ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በክልሉ ወስጥ ከአሁን በፊት የተገነቡም ሆነ በመገንባት ላይ ያሉ ዘመናዊ የመስኖ ተቋማትን አጠቃላይ ቆጠራ ለማካሄድ ከዩንቨርስቲው የቴክኖሎጂ ኢንስትቲውት ኋላፊ በሆኑት በዶ/ር ምትኩ ዳምጤ እና የክልሉ የመስ/ቆ/አካ/ል/ቢሮ ኋላፊ በሆኑት በዶ/ር-ኢ ዳኝነት ፈንታ መካከል የስምምነት ሠነድ የፊርማ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።
በስምምነቱ ውል መሠረት የባ/ዳር ዩኒቨርስቲ :-
🎯ሁሉንም ዘመናዊ መስኖ ተቋማት መዝግበው ለፖሊሲ አውጭዎች በሚያመች መልኩ የተተነተ የዳታ ቤዝ የመረጃ ስርዓት ለመገንባት ፣
🎯 በተቋማቶቹ ላይ የሚስተዋሉ በጥናት የተደገፈ ተጨባጭ በመስኖ ፕሮጀክት ሥራዎቾ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን እና በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት አማራጭ ሳይንሳዊ ሃሳቦችን ለማቅረብ ፣
🎯 የመስኖ ፀጋዎቻችንን የበለጠ ለመጠቀም መልካም አጋጣሚዎችን እና የሚስተዋሉ እጥረቶችን በጥናት ለመለየት፣
🎯 በቀላሉ መጠቀም የምንችልባቸው ዘመናዊና ተስማሚ የመስኖ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለማበልፀግ ፣
የተስማሙ ሲሆን የክልሉ መስ/ቆ/ አካ/ ልማት ቢሮ በውሉ መሠረት ሥራዎች በጥራት መሠራታቸው ተረጋግጦ አስፈላጊ ሠነዶች መረከቡ ሲረጋገጥ ክፍያ ለመፈፀም በመስማማት ከዛሬ ሚያዚያ 22/2016 ጀምሮ ሥራ ለመጀመር ሁለቱ ተቋማት ሥምምነት በመፈራረም በይፋ ሥራ ጀምረዋል።
ዘገባው:- የመስ/ቆ/አ/ል/ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት ነው

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top