በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው ዙር የአመራርና የማኔጅመንት የመስክ ስምሪት ድጋፍ ተጠናቀቀ፡፡

በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው ዙር የአመራርና የማኔጅመንት የመስክ ስምሪት ድጋፍ ተጠናቀቀ፡፡

ባህርዳር

01/04/2017

የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው እና በበጋ መስኖ ስራዎች የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ላይ ያተኮረው የመስክ ስምሪት በሁሉም የስምሪት ቀጣናዎች ተጠናቋል፡፡

ቢሮው ከአሁን በፊት የሞያተኞችን ድጋፍ መነሻ በማድረግ በተለይ ከፍተኛ ችግር ባለባቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ወደ ስራ ሊያስገባ የሚችል የማኔጅመንት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ስምምነት ላይ በመድረስ በአራት ቀጠናዎች የመጀመሪያውን ዙር ድጋፍ አጠናቋል፡፡

ድጋፉ በዋናነት የበጋ መስኖ ውሃ ማሰባሰብ ስራችን አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ በመገምገም በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት እና ከአቅም በላይ ሆኖ የኮር አመራሩን ድጋፍ የሚሹ ችግሮችን ለይቶ ችግሮች የሚቀረፉበት እና የዘመኑ የመስኖ ፕሮጀክት ዕቅዶቻቸን በተሟላ መልኩ ወደ

ስራ ሊያስገባ የሚችል ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነበር፡፡

በመስክ ስምሪቱ ደቡብ ወሎ ዞን መስ/ቆ/አካ/ል/ መምሪያ አንዱ ሲሆን በዞኑ በኩታበር ወረዳ የሚገኘው የጃልያ መስኖ ፕሮጀክት ተጀምሮ ከ10 ዓመታት በላይ መጠናቀቅ ባለመቻሉ ምክንያት የአካባቢው ማህበረሰብ የቅሬታ ምንጭ የሆነ ፕሮጀክት የነበረ ሲሆን ቢሮው በ2015 በአዲስ መልክ ውል በያዘው መሰረት አሁን ላይ የደረሰበትን አፈጻጸም ለማየት ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮጀክቱ በቀጣይ 20 ቀናት ውስጥ የቀረው 314 ሜትር የካናል ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአርሶ አደሩ የበጋ መስኖ ዝግጁ የማድረግ ስራ ለመስራት ስምምነት ተደርሷል፡፡

በተመሳሳይ የሚሌ ኮትቻ 3 ፕሮጀክት በውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ተቋራጭነት እንዲሁም በልህቀት ዲዛይን ኮርፖሬት አማካሪነት የተጀመረ ከአንድ ሺህ በላይ ሄ/ር ማልማት አቅም ያለው ፕሮጀክት ቢሆንም ከፍተኛ የአፈጻጸም ችግር የገጠመው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአካባቢው አመራር እና በህ/ሰቡ መካከል ያለመተማመን ምንጭ የሆነ ፕሮጀክት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዞን ዋና አስተዳዳሪ እና ም/አስተዳደሪ እንዲሁም የሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ተቋራጭ እና አማካሪ ተወካዮች በተገኙበት መድረክ በማመቻቸት በቀጣይ ጥቂት ጊዜቶች ውሃ ስራዎች ሁሉንም አይነት ግብዓትቶች ማጠናቀቁን እና ለሥራ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ያረጋገጠበትን የመነሻ ሃሳብ መሰረት ውይይት ተደርጎ ስምምነት ተደርሷል።

ተቋራጩ በአካባቢው ማህበረሰብ የመልማት ጥያቄ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ፕሮጀክት መሆኑ ተረድቶ ቅሬታዎች በየደረጃው ከመግፋታቸው በፊት ውሃ ስራዎች በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሊገባ እንደሚገባው ከሶሻል አንፃርም ሆነ መሠል ችግሮች የትኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርጉ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ያሳሰቡ ሲሆን በተመሳሳይ የአብክመ መስኖ ቆ/አካ/ል/ቢ/አማካሪ የሆኑት አቶ መለሰ ስንታየሁም እንደ አሰሪ መ/ቤት ፕሮጀክቱ በዕቅዱ መሰረት ይፈጸም ዘንድ ማንኛውንም ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ በቢሮው ስም አረጋግጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ስምሪቱ ከተቋማዊ ድጋፍ ባሻገር በመቋረጣቸው የማህ/ሰብ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሊቀጥሉ በሚችሉበት መንገድ ላይ ያተኮረ የተጠናከረ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የመስክ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ስምሪት በሌሎች ዞኖችም እንደሚቀጥል ስምምነት ተደርሷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top