በቢሮው የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም ፕሮጀክቶች የተገኘው ውጤት በአስቸጋሪ ሁኔታም መሰራት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደባቸው መሆኑ ተገለፀ።

በቢሮው የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም ፕሮጀክቶች የተገኘው ውጤት በአስቸጋሪ ሁኔታም መሰራት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደባቸው መሆኑ ተገለፀ።

ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም (መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ) በፕሮግራሙ ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ማጠቃለያ የቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ኢ/ር ዳኝነት ፈንታ እንደገለፁት የተገኙ ውጤቶች ቢሮው በአስቸጋሪ ሁኔታም መሰራት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደባቸው ናቸው ብለዋል።

ለአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ መነሻ በሆነው የመስክ ምልዕከታ የተሳተፊት የአስተባባሪ ዩኒቱ አመራር አቶ ሙላት ተካ በበኩላቸው እንደገለፁት በመስክ ምልከታውን የታዘብነው ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ያሉት በአስቸጋሪ ሁኔታ ቢሆንም በመልካም አፈፃፀም የሚገኝ መሆኑን መታዘብ ችለናል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በተጠናቀቁ የመስኖ አውታሮች አማካኝነት አርሶአደሮች ምርት ማምረት መጀመራቸውን መታዘብ መቻላቸውን ገልፀዋል።

በግምገማው የተሳተፉ ተቋራጮች መካከል አቶ አግሟስ ዋለ የተባሉት እንደገለፁት ውል የያዙት ፕሮጀክት በጣም ሩቅ መሆን፣ የሰው ሀይል ና ማቴሪያል ለማጓጓዝ አለመቻል ፣ የፀጥታ ችግር ፣ የዋጋ ንረት የመሳሰሉት ያጋጠሙን ችግሮች ቢሆኑም እስከ መጋቢት 2017 ዓም ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ እየሰራን እንገኛል ብለዋል።

በተመሳሳይ በግምገማ መድረኩ የተሳተፉ ሌሎች ተቋራጮችም ውል የወሰዱባቸው ፕሮጀክቶች ያጋጠሟቸውን ችግሮች አንድ በአንድ ገልፀው ከተገመገመ በኋላ ችግሮችን ፈተው ፕሮጀክቶች የሚያጠናቅቁበት የጊዜ ገደብ ያስቀመጡ ሲሆን ነባር ፕሮጀክቶች እስከ ጥር 30 አዲስ ፕሮጀክቶች ግንቦት 30/2017 እንደሚያጠናቅቁ በማረጋገጥ ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ የርዕስ መስተዳደሩ የሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካሪ አቶ ባዝዘው ጫኔ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ የግንባታ ፕሮጅክት አካለባቸው ቢሮዎች መካካል መስኖና ቆላማ አከባባዊዎች ልማት ቢሮ በተሸለ የአፈፀፃም እና ጥራት ደረጃ ላይ ያለ ቢሮ መሆኑን ገልፀው ነግር ግን ፕሮጀክቶ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ በኩል በተለይ በተቋራጮች ክትትልና ድጋፍ ማነስ ምክንያት የሚከሰ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ኢ/ር ዳኝነት ፈንታ እንደገለፁት የማስተባበሪያ ዩኒቱ አመራሮች እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ድጋፍ እና ክትትል ለተገኘው ውጤት ሚናቸው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ፊዚካል የፕሮጀክቶች አፈፃፀም መልካም ቢሆንም ፋይናሻል አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጅክቶች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የቢሮ ኃላፊው በፕሮግራሙ የሚሰሩ የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም በአብዛኛው መልካም ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ደካማ አፈፃፀም ያላቸውን ነባር ፕሮጀክቶች በያዝነው ዓመት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ተቋራጮች በመድረኩ በገቡት ቃል መሠረት የድርጊት መርሃግብር ከልሠው በማዘጋጀት በአምስት ቀን ውስጥ ዝርዝር ዕቅዳቸውን ለቢሮው እንዲያሳውቁ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም ከመስኖ ና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ጋር አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገና የውሃ ፖምፕ ሰርጭት እና የመስኖ ተጠቃሚዎች ማህበራት በሟቋቋም እና የማጠናከር ሥራ እየሰራ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top