በቢሮው አመራርና ማኔጅመንት አባላት የተደረገው የመስክ ድጋፍ ስምሪት የፕሮጀክት አፈፃፀም ችግሮችን በመፍታት በኩል ውጤታማ እንደነበር ተገመገመ፡፡

በቢሮው አመራርና ማኔጅመንት አባላት የተደረገው የመስክ ድጋፍ ስምሪት የፕሮጀክት አፈፃፀም ችግሮችን በመፍታት በኩል ውጤታማ እንደነበር ተገመገመ፡፡

ታህሳስ 8/2017 (ባህርዳር)

አብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የመጀመሪያው ዙር የመስክ ስምሪት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ታህሳስ 07/2017 ዓ.ም በጥልቀት ግምግሟል፡፡ በአራት ቀጠና ስምሪት የወሰደው ቡድን የተሰጣቸውን ቼክሊስት መሰረት አድርገው የተጠቃለለ ሪፖርት በመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን በእያንዳንዱ ዞን በጥንካሬ እና በድክመት እንዲሁም በቢሮው በኩል መፈታት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ግምገማ አድርጓል፡፡

በመድረኩ በተለይ ከመስኖ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን፣ ግንባታ እና የተቋማት አስተዳዳር ስራዎቻችን አፈጻጸም አንጻር በተለይ የማህ/ሰብ ቅሬታ በመፍጠር የመልካም አስተዳዳር ችግር የሆኑ የዋሉ ያደሩ ፕሮጀክቶቻችን ዙሪያ ችግሮች በሚፈቱበት ላይ ያተኮረ ጥልቀት ያለው ግምገማ ተኳሄዷል፡፡

ከዚህ አንጻር በማዕ/ጎንደር ዞን ለምስራቅ በለሳ፣ ለጎንደር ዙሪያ፣ ለወገራ መስኖ ፕሮጀክቶች መጓት ቁልፍ ችግር የተለየ ሲሆን በፊደራል በጀት የሚሰሩ የመገጭ ሰራባም ቢሆን ምንም አንኳን ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በአዲስ መልክ ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም በሙሉ አቅሙ በመስራት በኩል ውስንነት እንዳለ የገለጹት የቡድኑ አስተባባሪ እና የቢሮው

ም/ሃላፊ አቶ አየልኝ መሳፍንት የግምገማ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የሰ/ሸዋ ዞን ስምሪት አስተባባሪ እና የቢሮው ም/ሃላፊ በሆኑት ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ የሚመራው ቡድን በቀረበው የመስክ ሪፖርት በዞኑ የመስ/ቆ/አካ/ል/መምሪያ እና በዞኑ ግብርና መምሪያዎች መካካል ያለው የጋራ ቅንጅታዊ አሰራር በእጅጉ የሚበረታታ ሆኖ ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ የዋሉያደሩ አንስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አውቀው በትኩረት መስራት እንደሚገባ በመተማመን በተለይ የወረዳ ጽ/ቤቶችን በማጠናከር በኩል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ መካሻው ጋር የተደረገው ውይይትና የተደረሰው ስምምነት በጣም ጥሩ መሆኑን ማኔጅመንቱ ግምግሟል፡፡

በደ/ወሎ ዞን በአቶ መለሰ ስንታየሁ የቢሮው አማካሪ አስተባባሪነት የተመራው ቡድን ደግሞ የመስኖ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ሳይት ወርዶ በማረጋገጥ በኩታበር ወረዳ በመገኘት ከኢንተርፕራይዞች ያሉ ችግሮችን በምክክር መፍታት እና ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ በጥሩ የተገመገመ ሲሆን በተለይ የዞን ዋና አስተዳዳሪ እና ም/አስተዳዳሪዎች በተካፈሉበት መድረክ የሚሌ ኮትቻ ፕሮጀክት ከተቋራጭ አኳያ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ችግሮችን በጥልቀት መገምገም መቻሉ ቢሮው በቀጣይ በተቋራጩ ውሃ ስራዎች ድርጅት ጋር ስሚኖረን የውል ግንኙነት የግምገማ መነሻ ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም ችግር ፈች ክትትልና ድጋፍ ቡድኑ ማድረጉን ስምምነት ተደርሷል፡፡

በመጨረሻም የሰሜን ወሎ ዞን ቀጣና አስባባሪ የሆኑት አቶ አዳነ አልቃዲር (ዳሬክተር) አጠቃላይ የዞኑን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በቆቦ ጊራና ፕሮጀክት ማስተባባሪያን ስራዎች በአካል መጎብኘት መቻሉና በዞኑ ቢሮው እንዲፈታላቸው የቀረቡ ጥያቄዎችን አንድበአንድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ እንዳሉት በአመራርና ማኔጅመንት አባላት የተደረገው የመጀመሪያው ዘር የመስክ ድጋፍ ስምሪት የተቋሙን ማነቆዎች በመፍታት በኩል የተደረገው ጥረት ውጤታማ እንደነበር ጠቁመው ቡድኑ ከዞን መምሪያዎች ወርደው ወረዳ አልፎም ሳይት ወርደው ፕሮጀክት አይቶ ሞያዊ ድጋፍ ለመስጠት የተወሰደው ቁርተኝነት የሚበረታታ መሆኑን እና ለአጠቃላይ ሞያተኞቻችንም መነሳሳተን የሚፈጥር ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ሆኖ ዝርዝር የግምገማ ሃሳቡ በጽሁፍ ለዞን መምሪያዎች ግብረመልስ እንዲደርስ በመስማማት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top