የአንገረብ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት የጥናትና ዲዛይን ሥራ በያዝነው ዓመት መጠናቀቅ በሚችልበት መንገድ ላይ በአጋር አካላት የምክክር መድረክ የጋራ ሥምምነት ተደረሠ።

የአንገረብ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት የጥናትና ዲዛይን ሥራ በያዝነው ዓመት መጠናቀቅ በሚችልበት መንገድ ላይ በአጋር አካላት የምክክር መድረክ የጋራ ሥምምነት ተደረሠ።

ታህሳስ 09/2017 ዓም

ጎንደር

በአማራ ክልል በፌደራል መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚንስቴር በጀት ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች መካከል የአንገረብ መስኖ ግድብ አንዱ እንደመሆኑ ፕሮጀክቱ በታቀደለት መሠረት እንዳይፈፀም ያደረገውን የአካባቢ የፀጥታ ችግር ተሻግረን በያዝነው ዓመት ጥናትና ዲዛይን ሥራው ተጠናቆ ለግንባታ ርክክብ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ የአጋር አካላት የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ተካሄዷል።

በመድረኩ ከፌደራል ከፍተኛ የሥራ መሪዎች ፣ ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ ዋና አስዳዳሪዎች እና ፕሮጀክቱ ከሚነካቸው የማዕ/አርማጭሆ፣ የጠገዴ፣ የታች አርማጭሆ እና የምዕ/አርማጭሆ የተወከሉ የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ፕሮጀክቱ ያለበትን የጥናትና ዲዛይን ሥራ እና ለአካባቢው ማህበረሠብ ይዞ በሚመጣው በረከቶች ዙሪያ በመወያየት አሁን ላይ በፀጥታ ችግር ምክንያት የስራ መሳሪያዎችን በማጓጓዝም ሆኖ ሞያተኛ በማሠማራት በኩል ያሳደረው ተፅዕኖ የጥናትና ዲዛይን ሥራው አፈፃፀሙ 30% እንዳይሻገር ማድረጉን እና በዚህም ተቋርጦ መቆየቱን በመግለፅ በያዝነው 2017 ሚንስቴር መ/ቤቱ ፕሮጀክቱ የዞን አስተዳደሩ እና በየደረጃው ያለው አመራር እንዲሁም ከሁሉም በላይ ባለቤት የሆነው የአካባቢው ማህበረሠብ ማገዝ ከቻለ ፕሮጀክቱን በጊዜ የለኝም መንፈስ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ለመፈፀም ሚንስቴር መ/ቤቱ ማቀዱን በመግለፅ ፕሮጀክቱ የሃገራችን ድህነትን ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ውስጥ በስትራቴጅ ከያዛቸው ትልቁ መስኖ ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን በመጠቆም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የመስ/ቆላማ አካ/ሚንስቴር የፕሮጀክት ዘርፍ የሥራ መሪ የሆኑት ኢ/ር ያሬድ ሙላት የውይይት መነሻ አቅርበዋል።

በውይይት መድረኩ ጠቀሜታውን እንደሚረዱ በመግለፅ ፕሮጀክቱ ይነካቸዋል ተብለው በታሠቡ ከእምነት ቦታና የፀበል ቦታ ጋር ተያይዞ ከአሁን በፊት በመመካከር እንደማይነካቸው መግባባት ቢደረስም አሁንም አጀንዳ አድርገው ህ/ሰቡን የሚያወናብዱ አካላት መኖራቸው ታውቆ ህዝባችንን በማስተማር በኩል የድርሻችንን እንወስዳለን ያሉት የአካባቢውን ማህ/ሰብ ወክለው የተገኙት ሽማግሌዎች ናቸው።

በተመሳሳይ ወረዳዎችን ወክለው የመጡት ዋና አስተዳዳሪዎች እንዳሉት በህዝብ መድረኮቻችን ሁሉ የሚነሳው ትልቁ አጀንዳ አንገረብ መሆኑን በመግለፅ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሙሉ በመመካከር እንደሚፈቱትና ፕሮጀክቱ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባላቸው ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የማዕ/ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ በማጠቃለያ ሃሳባቸው እንዳሉት ለፕሮጀክቱ የሥራ መሳሪያዎች የተባሉትን ጎንደር ከተማ ከደረሱ በኋላ ሙሉ ሃላፊነቱን እንደሚወስዱ በማረጋገጥ ነገ ዛሬ ሳይባል ወደ ሥራ እንዲገባና ለህዝባችን በሚኖረው ጠቀሜታ ልክ ከየትኛውም ሥራቸው ቀዳሚ አድርገው እንደሚፈፅሙት ገልፀዋል።

አክለውም አቶ አወቀ እንዳሉት ከእምነት ተቋማትም ሆነ ከፀበል ሥፍራ ጋር የሚነሱ አጀንዳዎችን ሃይማኖት የትውልድ መሠረት እንደመሆኑ የህዝብን ጥያቄ በማክበር የማልማት አቅሙን ከ50ሺህ ሄ/ር ወደ 21 ሺህ ሄ/ር በመቀነስ ምላሽ ከሚንስቴር መ/ቤቱ የተሰጠበት ሆኖ ሳለ ፕሮጀክቱ እንዳይፈፀም በሚሰሩ ፀረ ልማት ሃይሎች ካሉ ህዝባቸውን ይዘው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በማጠቃለያም በሚ/ር መስሪያቤቱ የሚመራ የሁሉንም ወረዳ አስተዳዳሪዎች እና አማካሪ ድርጅቱ የተካተተበት አብይ ኮሚቴ በማዋቀር በተመሳሳይ በየወረዳው ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅቶ በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመራ በማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ሥራ እንዲገባ የጋራ ሥምምነት ተደርሷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top