“የመስኖ ኘሮጀክቱ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
የካቲት 09/2017 ዓ.ም የአማራ ክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ ከጎበኟቸው የልማት ሥረዎች “የግድቡት” የመስኖ ኘሮጀክት አንደኛው ነው። የመስኖ ፕሮጄክቱ 14 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ያለማል። ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎበታል ነው የተባለው።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የመስኖ ኘሮጀክቱ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል። ግድቡ ረዘም ላሉ ዓመታት አገልግሎት መስጠት እንደሚችልም ተገልጿል።
ያስመረቅነው የመስኖ ፕሮጀክት የአመራር እና የህዝብ ትብብር የተገለጸበት እና የአርሶ አደራችንን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ” ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር- ኢ/ር). በጉብኝቱ የተገኙት የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደገለጹት የተገነባውን የመስኖ ፕሮጀክት በደለል እንዳይሞላ የጥበቃ ስራዎችን በመስራት እና የተቋቋመውን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር በማጠናከር በሙሉ አቅም ወደ ልማት በማስገባት የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ማረጋጋጥ የሚገባ መሆኑን በመግለጽ ሰላምን በዘላቂነት ለማጽናት በሚደረገው ጥረት ህዝቡ ተባባሪ እንድሆንም መልእክት አስተላልፈዋል። ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በዞኑ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች እየተመለከቱ ነው።



